Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፥ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፣ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ ውርደታችንን አስቀርልን!” ይሉታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚ​ያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እን​ጀ​ራ​ች​ንን እን​በ​ላ​ለን፤ የገዛ ልብ​ሳ​ች​ን​ንም እን​ለ​ብ​ሳ​ለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰ​ደ​ባ​ች​ን​ንም አር​ቅ​ልን” ብለው አን​ዱን ወንድ ይይ​ዙ​ታል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 4:1
15 交叉引用  

ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ አለች፤


የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፥ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።


የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፥ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።


በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፥ ዓይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።


ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፥ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፥ የሰውም ኵራት ይወድቃል፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፦ አንተ ልብስ አለህ አለቃም ሁንልን ይህችም ባድማ ከእጅህ በታች ትሁን ሲለው፥


አታፍሪምና አትፍሪ፥ አትዋረጂምና አትደንግጪ፥ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።


መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፥ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፥ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።


የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።


እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን።


እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበርና ጣውንትዋ ታስቆጣት ታበሳጫትም ነበር።


跟着我们:

广告


广告