Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 39:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያን ዘመን የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ መዳኑን ሰማ፤ ስለዚህም ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 39:1
11 交叉引用  

ዳዊትም፦ አባቱ ወረታ እንዳደረገልኝ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው ባሪያዎቹን ላከ፥ የዳዊትም ባሪያዎች ወደ አሞን ልጆች አገር መጡ።


ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ድል ስለ መታ ቶዑ ልጁን አዶራምን ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ፥ ይመርቀውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፥ እርሱም የብርና የወርቅ የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።


ብዙዎቹም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፤ ልቡም ኳራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቍጣ ሆነ።


ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በአገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተናገረ ሸክም።


እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።


ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ እንዲህም ትላለህ፦ አስጨናቂ እንዴት አረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!


እነሆ፥ የከለዳውያን አገር! ይህ ሕዝብ ሆኖ አይገኝም፥ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል፥ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፥ ባድማም አደረጓት።


跟着我们:

广告


广告