Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፦ እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ባለ መድኃኒት አልሆንም፥ በሕዝቡም ላይ አለቃ አታደርጉኝም ይላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እርሱ ግን በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኔ መፍትሒ አልሆንም፤ በቤቴም ልብስና ምግብ የለኝም፤ የሕዝብ መሪ አታድርጉኝ” ይላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርሱ ግን በዚያ ቀን ድምጽን ከፍ አድርጎ፤ “እኔ መፍትሔ አልሆንም፤ በቤቴም ልብስና ምግብ የለኝም፤ የሕዝብ መሪ አታድርጉኝ” ይላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እርሱም በዚያን ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ “እኔም ብሆን በቤቴ ውስጥ የበቃ ምግብም ሆነ ልብስ ስለሌለኝ መፍትሔ ላስገኝላችሁ አልችልም! ስለዚህ መሪ አታድርጉኝ!” ሲል ይመልስላቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በዚያ ቀን ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እን​ጀራ ወይም ልብስ የለ​ኝ​ምና ለሕ​ዝቡ አለቃ አል​ሆ​ንም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 3:7
10 交叉引用  

አብራምም የስዶምን ንጉሥ አለው፤ ሰማይንና ምድርን ወደ ሚግዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤


ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፥ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድ አዳሽ ትባላለህ።


በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?


የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፥ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቍስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።


ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፥ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፥ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።


ከዓይናችን ፊት ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋ አይደለምን?


እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ 2 እንዲህም እላለሁ፦ ለዘላለም እኔ ሕያው ነኝና


跟着我们:

广告


广告