Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የአምሳ አለቃውንም፥ ከበርቴውን፥ አማካሪውንም፥ ብልሁንም ሠራተኛ፥ አስማት አዋቂውንም ይነቅላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የዐምሳ አለቃውንና ባለማዕርጉን፣ አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለሙያ፣ ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፤ አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለሙያ፤ ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ምሳ አለ​ቃ​ው​ንም፥ የተ​ከ​በረ አማ​ካ​ሪ​ው​ንም፥ ጠቢ​ቡ​ንም፥ የአ​ና​ጢ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ፥ አስ​ተ​ዋይ አድ​ማ​ጩ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 3:3
11 交叉引用  

በክንድ የበረታ ምድርን ገዛ፥ ከበርቴውም ሰው ተቀመጠባት።


አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።


ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ጌታ ሆይ! እኔ አፌ ኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም።”


ኃያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነብዩንም፥ ምዋርተኛውንም፥ ሽማግሌውንም፥


አለቆቻቸው እንዲሆኑ ብላቴኖችን አስነሣባቸዋለሁ፥ ሕፃናቶችም ይገዙአቸዋል።


ስለዚህ ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፥ ጌታን አላወቁትምና፥ ከበርቴዎቻቸውም ተራቡ፥ ሕዝባቸውም ተጠሙ።


ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፥ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች መረጥሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች የሻለቆችም የመቶ አለቆችም የአምሳ አለቆችም የአሥር አለቆችም ገዦችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።


ዛብሄልና ስልማናን፦ በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ? አላቸው። እነርሱም፦ እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፥ አንተንም ይመስሉ ነበር፥ መልካቸውም እንደ ንጉሥ ልጆች መልክ ነበረ ብለው መለሱለት።


ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋቸዋል፥ እርሻውንም የሚያርሱ እህሉንም የሚያጭዱ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告