Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 27:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አልቈጣም፥ እሾህና ኵርንችት በእኔ ላይ ምነው በሰልፍ በነበሩ! በእነርሱ ላይ ተራምጄ በአንድነት ባቃጠልኋቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኔ አልቈጣም። እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ! ለውጊያ በወጣሁባቸው፣ አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እሾህና ኩርንችት ቢያበቅልብኝ፥ እኔ አልቈጣም፥ በእነርሱ ላይ ተራምጄ አቃጥላቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዳግመኛ በወይን ቦታዬ ላይ አልቈጣም፤ የወይን ቦታዬን የሚያበላሹ ኲርንችትና እሾኽ ቢኖሩ ነቃቅዬ በእሳት በማቃጠል ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 27:4
17 交叉引用  

ዓመፀኞች ሁሉ ግን ሰው በእጁ እንደማይዘው፥ እንደ ተጣለ እሾህ ናቸው።


ማናቸውም ሰው ይነካው ዘንድ ቢወደድ፥ በእጁ ብረትና የጦሩን የቦ ይይዛል፥ በሥራቸውም በእሳት ፈጽሞ ይቃጠላሉ።


የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፥ እሾሁንና ኵርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል ይበላውማል።


በዚያም ቀን፦ አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኽኛልምና አመሰግንሃለሁ።


አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፥ ተቆርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።


ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፥ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፥ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።


ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፥ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።


እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው።


ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤


跟着我们:

广告


广告