Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 26:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አቤቱ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ሆይ፤ በተጨነቁ ጊዜ ወደ አንተ መጡ፤ በገሠጽሃቸውም ጊዜ፣ በለኆሳስ ድምፅ ይጸልያሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አቤቱ ጌታ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አምላክ ሆይ! በችግራቸው ጊዜ ፈለጉህ በገሠጽካቸውም ጊዜ በጸሎት ወደ አንተ ተመለሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 26:16
23 交叉引用  

እነርሱም፦ ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፥ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ኃይል የለም።


ግንዱን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ ይላሉ፥ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ተነሥተህ አድነን ይላሉ።


አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ!


እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።


ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።


በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ ሄጄ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፥ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።


በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፥ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፥ በእኔም ላይ ዐመፁ።


ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፦ በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ገባ።


የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፦ እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፥ አንተ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፥ ዛሬ ግን፥ እባክህ፥ አድነን አሉት።


ሐናም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ፥ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፥


跟着我们:

广告


广告