Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም፥ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፥ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤ በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ክፉዎች እድል ቢሰጣቸው እንኳን ጽድቅን አይማሩም፤ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋሉ፥ የጌታንም ግርማ አያዩም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 26:10
36 交叉引用  

ነገር ግን በእርስዋ ሄዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም፤ ደግሞም የማምለኪያ ዐፀድ በሰማርያ ቆሞ ቀረ።


ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም።


ነገር ግን አንተና ባሪያዎችህ አምላክን እግዚአብሔርን ገና እንደማትፈሩ አውቃለሁ፤” አለው።


ፈርዖንም ዝናቡ በረዶውም ነጎድጓዱም እንደ ተቍረጠ ባየ ጊዜ ኃጢያትን ጨመረ፤ እርሱና ባሪያዎቹም ልባቸውን አደነደኑ።


ደግሞም ከፀሐይ በታች በፍርድ ስፍራ ኃጢአት፥ በጽድቅም ስፍራ ኃጢአት እንዳለ አየሁ።


በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።


ፍርድ ሞልቶባት የነበረው የታመነችይቱ ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፥ አሁን ግን ገዳዮች አሉባት።


ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።


ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች፥ ሕጉን ተላልፈዋልና፥ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፥ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሳደዱ ይመጣሉ፥ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።


ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፥ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስህተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል።


የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት፥ ችግረኛ ቅን ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳን እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል።


መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።


ፍሬዋንና በረከትዋንም ትበሉ ዘንድ ወደ ፍሬያማ ምድር አገባኋችሁ፥ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፥ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠርዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ አገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ፥ የቅድስና ተራራ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ የሚልን ነገር እንደ ገና ይናገራሉ።


ሕዝቤም ከእኔ ይመለሱ ዘንድ ወደዱ፥ ወደ ላይም ቢጠሩአቸው ማንም ከፍ ከፍ ያደርጋቸው ዘንድ አይችልም።


ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፥ ስለዚህ ረሱኝ።


በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፥ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኵስን ነገር ይበላሉ።


በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።


ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦


ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ 2 ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ 2 የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ 2 የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።


ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።


ሳሙኤልም አለ፦ በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።


跟着我们:

广告


广告