Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃልና፥ ይኸውም የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፥ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋራ አገና ይማታሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን፤ ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋር ተባብረዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አምላክ ሆይ! የያዕቆብ ዘሮች የሆኑ ሕዝብህን እርግፍ አድርገህ ትተሃል፤ ምድሪቱ በምሥራቅ አገር ሰዎች ጥንቈላና በፍልስጥኤማውያን ሟርት ተሞልታለች፤ ሕዝቡም ከአሕዛብ ጋር ተባብረዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 2:6
31 交叉引用  

አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም “ሂዱ፤ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ፤” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።


እግዚአብሔርም የእስራኤልን ዘር ሁሉ ጠላ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።


እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ።


አሳንም ሊያገኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆመና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካምም አይሆንላችሁም፤ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል’” አላቸው።


ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።


መተተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድላት።


ሴት ልጆቻቸውንም ከወንድ ልጆችህ ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።


ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።


እነርሱም፦ የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፥ አሕዛብ ይፈሩታልና።


ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።


ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?


ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቍዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቍዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


የምድርህንም ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈርሳለሁ፥


መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥


በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ።


ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ ብሎ።


መልካም፤ እነርሱ ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ አንተም ከእምነት የተነሣ ቆመሃል። ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ።


ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠርተው፥ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራውስ በምን እንስደደው? አስታውቁን አሉ።


跟着我们:

广告


广告