Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 መልእክተኞችን በባሕር ላይ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነው ወገን፥ ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት። እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ረዣዥምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ያቺ አገር መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ትልካለች፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፥ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፥ ጠንካሮችና ኀያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በባ​ሕር ላይ፥ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም በውኃ ላይ ይል​ካል። ፈጣ​ኖች መል​እ​ክ​ተ​ኞች ወደ ረዥ​ምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄ​ዳ​ሉና፤ ተስፋ የቈ​ረ​ጡና የተ​ረ​ገጡ ሕዝብ እነ​ማን ናቸው? ዛሬ ግን የም​ድር ወን​ዞች ሁሉ፥ ሰዎች እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ሀገር ይኖ​ራሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 18:2
14 交叉引用  

ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ።


ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው።


የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል።


ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።


በዚያን ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ከሆነ ወገን፥ ከሚሰፍርና ከሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ እጅ መንሻ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም ወደሚገኝበት ስፍራ ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።


ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።


በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፥ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፥ እነሆ፥ ይመጣልና።


የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ ብሎአል።


እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፥ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል።


እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።


跟着我们:

广告


广告