Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ተወገደች የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣ የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤ የሶርያም ትሩፍ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል፤ ይላል የሠራዊት ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እስራኤል ያለ መከላከያ ትቀራለች፤ ደማስቆም ነጻነትዋን ትገፈፋለች፤ ከጥፋት የተረፉ እነዚያ ሶርያውያን እንደ እስራኤል ሕዝብ የተዋረዱ ይሆናሉ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኤፍ​ሬም የሚ​ጠ​ጋ​በት ምሽግ አይ​ኖ​ርም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ንጉሥ በደ​ማ​ስቆ አይ​ነ​ግ​ሥም። የሶ​ርያ ቅሬታ ሆይ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከክ​ብ​ራ​ቸው የም​ት​ሻል አይ​ደ​ለ​ህም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 17:3
27 交叉引用  

የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ በደማስቆ ላይ ወጣባት፤ ወሰዳትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለ።


በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ወሰደ፤ እስራኤልንም ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።


ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?


አሁን ግን እግዚአብሔር፦ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፥ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል ይላል።


በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የያዕቆብ ክብር ይደክማል የሥጋውም ውፍረት ይከሳል።


ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፥ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፥ የኀጥኣንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፥ ከቶ አትሠራም።


ሕፃኑም ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።


የሶርያ ራስ ደማስቆ ነው፥ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፥ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም፥


እግዚአብሔርም፦ ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ።


እግዚአብሔርም፦ ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፥


ደግሞ ፀነሰች ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፦ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምርምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፥


በሕዝብህም መካከል ሽብር ይነሣል፥ እናትም ከልጆችዋ ጋር በተፈጠፈጠች ጊዜ ሰልማን ቤትአርብኤልን በሰልፍ ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፥


እስራኤል ተውጦአል፥ በአሕዛብ መካከል ዛሬ እንደ ረከሰ ዕቃ ሆኖአል።


የኤፍሬምም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፥ መውለድና መፅነስ ማርገዝም አይሆንላቸውም።


በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉና፦ ዳን ሆይ፥ ሕያው አምላክህን! ደግሞ፦ ሕያው የቤርሳቤህን መንገድ! ብለው የሚሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ደግሞም አይነሡም።


跟着我们:

广告


广告