Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ፥ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፥ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የሞዓባውያን ስደተኞች ከእናንተ ጋራ ይቈዩ፤ እናንተም ከአጥፊው መጠጊያ ሁኗቸው።” የጨቋኙ ፍጻሜ ይመጣል፤ ጥፋቱ ያከትማል፤ እብሪተኛም ከምድር ገጽ ይጠፋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ዘንድ ይኑሩ፤ ስደተኞቹን ከሚሳድዷቸው መሸሸጊ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፤ ጨቋኞች የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሞአብ ስደተኞች በመካከላችሁ ይኑሩ፤ ሊያጠፉአቸው ከሚፈልጉ ወገኖች መጠጊያ ሁኑአቸው።” ጨቋኞች ከእንግዲህ ወዲያ አይኖሩም፤ ያገር መፈራረስም ያከትማል። ወራሪዎችም ይወገዳሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሚ​ከ​ቧ​ችሁ ጋር ጠላ​ቶች እን​ዳ​ይ​ሆ​ኗ​ችሁ ከሞ​ዓብ የተ​ሰ​ደ​ዱ​ትን ከእ​ና​ንተ ጋር አታ​ስ​ቀ​ምጡ፤ ሰል​ፈ​ኞች አል​ቀ​ዋ​ልና፤ በሀ​ገ​ሪቱ ሁሉ የነ​በ​ረ​ውም አለቃ ጠፍ​ቶ​አ​ልና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 16:4
22 交叉引用  

ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ እንዲህም ትላለህ፦ አስጨናቂ እንዴት አረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!


የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፥ ሣሩም ደርቋል፥ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።


የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፥ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፥ መወንጀልንም በተውህ ጊዜ ይወነጅሉሃል።


አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።


ሰማያትንም የዘረጋውን ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ረስተሃል፥ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁል ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፥ የአስጨናቂው ቍጣ የት አለ? ምርኮኛው ፈጥኖ ይፈታል፥


በጽድቅ ትታነጺያለሽ፥ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።


እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


በምድያም ጊዜ እንደሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር ያስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።


የዳዊት ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።


በሞዓብም በአሞንም ልጆች መካከል በኤዶምያስም በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ፥


በዲቦን የምትኖሪ ሆይ፥ ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በጥማትም ተቀመጪ።


እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፥ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል።


የሸሹትንም ለመግደል በመንታ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ፥ በጭንቀትም ቀን ከእርሱ የቀሩትን አሳልፈህ ትሰጥ ዘንድ አይገባህም ነበር።


በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።


እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፥ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


ድሀና ችግረኛ የሆነውን ምንደኛ፥ ከወንድሞችህ ወይም በምድርህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚቀመጡት መጻተኞች ቢሆን፥ አታስጨንቀው።


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


跟着我们:

广告


广告