Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ይሰማል፥ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፥ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ ልባቸውም ራደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ፥ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ተሰማ፤ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍሱም ራደች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሐሴቦንና የኤልዓሌ ሕዝቦች ይጮኻሉ፤ የጩኸታቸውም ድምፅ እስከ ያሐጽ ድረስ ይሰማል፥ የሞአብ ወታደሮች ሳይቀሩ ወኔያቸው ከድቶአቸው በፍርሃት ተርበደበዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 15:4
19 交叉引用  

ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?


እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና “ይበቃኛል፤ አሁንም፥ አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ፤” ብሎ እንዲሞት ለመነ።


ድካምንና ጣርን አይ ዘንድ ዘመኔም በእፍረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማኅፀን ወጣሁ?


በሜዳ ላይ፥ በሖሎን፥ በያሳ፥ በሜፍዓት ላይ፥


ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፥ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፥ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።


እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህች ክፉ ወገን የተረፉ ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ።


እንዲህስ ከምታደርግብኝ፥ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፥ በእኔ ላይ የሚሆነውን መከራ እንዳላይ፥ እባክህ፥ ፈጽሞ ግደለኝ።


ሴዎንም እስራኤል በምድሩ ላይ ያልፍ ዘንድ እንቢ አለ፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፥ ወደ ያሀጽም መጣ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።


እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤


ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ።


ቤትባኣልምዖን፥ ያሀጽ፥ ቅዴሞት፥


በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ አያገኙትምም፥ ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።


ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም ነበር፥ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ በያሀጽም ሰፈረ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ።


跟着我们:

广告


广告