Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፥ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዝዛለሁ፤ ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ ቁጣዬንም እንዲፈጽሙ፤ ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቊጣዬን ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዤአለሁ፤ ድሌ የሚያስደስታቸውን ኀያላኔን ጠርቼአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 13:3
20 交叉引用  

በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ መንግሥታትንም አናወጠ፥ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ።


ለአሕዛብም በሩቅ ምልክትን ያቆማል፥ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፥ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ ልባችሁም የዛለ አይሁን፥ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፥ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፥ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፥ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።


ባቢሎን ምንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ የኃይልዋንም ከፍታ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።


እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ቸኵላችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ አቤቱ፥ ኃያላኖችህን ወደዚያ አውርድ።


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ።


ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።


跟着我们:

广告


广告