ኢሳይያስ 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፥ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፥ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ በእጅ ጥቀሱ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፣ በእጅ ምልክት ስጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፤ በእጅ ምልክት ስጡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ምንም ነገር በማይበቅልበት ተራራ ጫፍ ሆናችሁ ምልክት ስጡ፤ ወደ ትዕቢተኞቹ የባቢሎን ገዢዎች ወደሚያስገባው በር እንዲገቡ ትእዛዝ ስጡ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጉባቸው፤ አለቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮችንም ክፈቱ። 参见章节 |