Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፥ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤ ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤ ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጉድጓድ ይከትታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጡት የሚጠባው ሕፃን በእባብ ጒድጓድ አጠገብ ይጫወታል፤ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኚት ቤት ላይ እጁን ያኖራል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሚ​ጠ​ባ​ውም ሕፃን በእ​ባብ ጕድ​ጓ​ድና በእ​ፉ​ኝት ቤት ላይ እጁን ይጭ​ናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 11:8
7 交叉引用  

ቃል ኪዳንህ ከምድረ በዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና፥ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።


ላምና ድብ አብረው ይሰማራሉ፥ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።


በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፥ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።


ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።


የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፥ እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።


跟着我们:

广告


广告