Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከእስረኞች በታች ያጐነብሳሉ፥ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:4
19 交叉引用  

ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፥ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፥ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።


ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፥ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይጎበኛሉ።


ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። የሬሳቸውም ግማት ይሸታል፥ ተራሮችም ከደማቸው የተነሣ ይርሳሉ።


ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፥ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፥ ሬሳቸውም በአደባባይ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኗል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፥ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሳበታል፥


ጠላቶቹም ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፥ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳን ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፥ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።


ሰው ሁሉ ዝንጉና ክፉ ሠሪ ነውና፥ አፍም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና ስለዚህ ጌታ በጕልማሶቻቸው ደስ አይለውም፥ ለደሃ አደጎቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል ይራብማል፥ በግራም በኩል ይበላል አይጠግብምም፥ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፥


ምናሴ ኤፍሬምን ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፥ እነርሱ በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


እነርሱም፦ ወዴት እንውጣ ቢሉህ፥ አንተ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።


እናንተም የሚዋጉትን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ብትመቱት ኖሮ፥ ከእነርሱም የተወጉት ብቻ ቢቀሩ ኖሮ፥ ሁሉ እያንዳንዱ በድንኳኑ ተነሥቶ ይህችን ከተማ በእሳት ባቃጠሉአት ነበር።


የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ።


ልጆቻቸውንም ቢያሳድጉ ሰው እንዳይቀርላቸው ልጅ አልባ አደረጋቸዋለሁ፥ ከእነርሱም በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!


ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፥ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።


እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?


跟着我们:

广告


广告