Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በተጐበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:3
40 交叉引用  

ያዕቆብም የላባ ልጆች ያሉትን ነገር፦ ያዕቆብ ለአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ ይህንም ሁሉ ክብር ከአባታችን ከብት አገኘ ሲሉ ሰማ።


በኋላቸው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ሄዱ፤ እነሆም፥ ሶርያውያን ሲሸሹ የጣሉት ልብስና ዕቃ መንገዱን ሁሉ ሞልቶ ነበር። መልእክተኞችም ተመልሰው ለንጉሡ ነገሩት።


እግዚአብሔር በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ? በጐበኘኝ ጊዜ ምን እመልስለታልሁ?


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።


በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የያዕቆብ ክብር ይደክማል የሥጋውም ውፍረት ይከሳል።


በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፥ እኛስ እንዴት እናመልጣለን? ይላሉ።


እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፥ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፥ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምን ምን አድርገሃል።


በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፥ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።


ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፥ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያ ጠባብ ነው።


ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።


ነገር ግን፦ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፥ ደግሞም፦ በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።


ሁላቸው ይጠቅሟቸው ዘንድ ስለማይችሉ፥ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ።


የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምና ምን ነው፥ ስለዚህ ስሙን፦ በቤት የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ።


በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፥ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፥ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?


ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ? አለው። ሕዝቅያስም፦ ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ አለው።


ሲዖልም ሆድዋን አስፍታለች፥ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፥ ከበርቴዎቻቸውና አዛውንቶቻቸው ባለጠጎቻቸውም ደስተኞቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።


ለአሕዛብም በሩቅ ምልክትን ያቆማል፥ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፥ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።


መሣሪያም የሚይዙትን አጥፊዎች በአንተ ላይ አዘጋጃለሁ፥ የተመረጡትንም የዝግባ ዛፎችህን ይቈርጣሉ፥ በእሳትም ውስጥ ይጥሉአቸዋል።


አንቺም የተበዘበዝሽ ሆይ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኵል በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፥ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፥ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፥ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቍስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።


በዓመት በዓል ቀንና በእግዚአብሔር በዓል ቀን ምን ታደርጋላችሁ?


የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፥ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።


ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።


በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።


አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና።


እግዚአብሔር ቍንቍቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል።


ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


跟着我们:

广告


广告