Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፥ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የበቀል ወራት መጥቷል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ይወቀው፤ ከበደልህና ከጥላቻህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሞኝ ሆኗል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የቅጣት ቀን ደርሶአል፤ እስራኤላውያንም የበቀል ቀን መቃረቡን ይወቁ፤ በእናንተ በደልና ጥላቻ ምክንያት ነቢይን እንደ ሞኝ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደ ዕብድ ትቈጥሩታላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የበ​ቀል ወራት መጥ​ቶ​አል፤ የፍ​ዳም ወራት ደር​ሶ​አል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ አበደ ነቢ​ይና ርኩስ መን​ፈስ እንደ አለ​በት ሰው ይታ​መ​ማል፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህና ከጠ​ላ​ት​ነ​ትህ ብዛት የተ​ነ​ሣም ቍጣ​ህን አበ​ዛህ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 9:7
40 交叉引用  

ኢዩም ወደ ጌታው አገልጋዮች ወጣ፤ እነርሱም “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን መጣብህ?” አሉት። እርሱም “ሰውዮውንና ንግግሩን ታውቃላችሁ፤” አላቸው።


በተጐበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?


አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፥ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፥ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፥ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፥


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፥ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።


ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።


በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ፥ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤል ያስቱ ነበር።


ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እነርሱን ያስገዙአቸዋል፥ እኔም እንደ አደራረጋቸውና እንደ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።


እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በዛንጅር ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።


በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፥ የጥፋታቸው ቀንና የመጐብኘታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፥ በአንድነትም ሸሹ፥ አልቆሙምም።


የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፥ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፥ ሰላም ሳይሆን፦ ስለም ሰላም ይላሉ።


ኖን። ነቢያቶችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።


ሰላም ሳይኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፥ አንዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ፥ እነሆ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንምን ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉ ለሰነፎች ነቢያት ወዮላቸው!


በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ፥ በቀሌንም በላያቸው ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


ታላቅ እሆናለሁ እቀደስማለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


እኔም ደግሞ በዓይኔ አልራራም አላዝንምም፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ አለኝ።


እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።


ኤፍሬም በዘለፋ ቀን የፈረሰ ይሆናል፥ በእስራኤል ነገዶች ዘንድ በእርግጥ የሚሆነውን ነገር ገልጫለሁ።


መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፥ እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም፥ በደላቸውንም ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል፥ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


ኤፍሬም ከአምላኬ ጋር ተመልካች ነበረ፥ አሁን ግን ነቢዩ በመንገዱ ሁሉ ላይ የወፍ ወጥመድ ሆነ፥ በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለ።


እርሱም፦ አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፦ ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።


ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፥ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።


ዘመዶቹም ሰምተው፦ አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።


የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።


እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።


ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።


跟着我们:

广告


广告