Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ሄዱ፥ ግብጽም ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፥ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሳል፥ እሾህም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 9:6
32 交叉引用  

ለኢዮአካዝም ከአምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥርም ሠረገሎች፥ ከዐሥር ሺህም እግረኞች በቀር ሕዝብ አልቀረለትም፤ የሶርያ ንጉሥ አጥፍቶአቸዋልና፤ በአውድማም እንዳለ ዕብቅ አድቅቆአቸዋልና።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።


የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፥ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


በሕዝቤ ምድር ላይ፥ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፥


በአዳራሾችዋም እሾህ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፥ የቀበሮም ማደሪያና የሰጎን ሥፍራ ትሆናለች።


ባድማ አደርገዋለሁ፥ አይቆረጥም፥ አይኮተኮትም፥ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፥ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ሥፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ይሆናል።


የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች አስነወሩሽ አላገጡብሽም።


አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ።


በግብጽ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።


ወደ ግብጽም ይገቡ ዘንድ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፥ ሁሉም ይጠፋሉ፥ በግብጽም ምድር ይወድቃሉ፥ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፥ ለጥላቻና ለመደነቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።


ኢየሩሳሌምንም እንደ ቀጣሁ፥ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ።


በግብጽ ተናገሩ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፥ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።


አንቺ በግብጽ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ፥ ሜምፎስ ባድማ ትሆናለችና፥ ትቃጠልማለችና፥ የሚቀመጥባትም አይገኝምና ለምርኮ የሚሆን ዕቃ አዘጋጂ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ ምስሎችንም ከሜምፎስ እሽራለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ምድር አለቃ አይሆንም፥ በግብጽም ምድር ላይ ፍርሃትን አደርጋለሁ።


በግብጽም እሳትን አነድዳለሁ፥ ሲንም ትጨነቃለች ኖእም ትሰበራለች፥ በሜምፎስም በየቀኑ ጠላቶች ይሆኑባታል።


የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ እሾህና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፥ ተራሮችንም፦ ክደኑን፥ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን ይሉአቸዋል።


እንደ ወፍም ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፥ በቤታቸውም አኖራቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


በጥማትም እንዳልገድላት፥ የግልሙትናዋ ልጆች ናቸውና ልጆችዋን አልምርም።


ኤፍሬምም አእምሮ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፥ ግብጽን ጠሩ፥ ወደ አሦርም ሄዱ።


ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐምፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ ልታደጋቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ።


ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፥ እንደ ተንኰለኛ ቀስት ሆኑ፥ አለቆቻቸው ከምላሳቸው ቍጣ የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይህ በግብጽ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።


መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፥ እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም፥ በደላቸውንም ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል፥ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፥ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኵስን ነገር ይበላሉ።


እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።


እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።


ሕዝቡም ተጨንቀው ነበርና የእስራኤል ሰዎች በጭንቀት እንዳሉ ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋሻና በእሾህ ቁጥቋጦ በገደልና በግንብ በጉድጓድም ውስጥ ተሸሸጉ።


跟着我们:

广告


广告