Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፥ ደግሞም ቢወልዱ የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ኤፍሬም ተመታ፤ ሥራቸው ደረቀ፤ ፍሬም አያፈሩም፤ ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ኤፍሬም ተመታ፥ ሥሩም ደረቀ፥ ፍሬም አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ እንኳ እጅግ የሚወዱአቸውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእስራኤል ሕዝብ ነፋስ እንደ መታው፥ ሥሩ እንደ ደረቀና ማፍራት እንደማይችል ዛፍ ያለ ፍሬ ይቀራሉ፤ ልጆች ቢወልዱም እጅግ የሚወዱአቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 9:16
10 交叉引用  

ከእነርሱም በኍላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ስባት እሸቶች ወጡ


ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል።


ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፥ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፥ እነርሱም ደረቁ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው።


ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፥ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል ቡቃያቸውም እንደ ትብያ ይበንናል፥ የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።


ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁን ትምክሕት፥ የዓይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁን ምኞት መቅደሴን አረክሳለሁ፥ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


ኤፍሬም ከትእዛዝ በኋላ መሄድን ወድዶአልና የተገፋና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል።


ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፥ አገዳ የለውም፥ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፥ ቢገኝም እንግዶች ይበሉታል።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፥ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፥ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ጉልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 2 በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል።


跟着我们:

广告


广告