Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ይህ ደግሞ ከእስራኤል ዘንድ ነው፥ ሠራተኛ ሠራው፥ እርሱም አምላክ አይደለም፥ የሰማርያም እምቦሳ ይቈራረጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይህም በእስራኤል ሆነ! የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክ አይደለም፤ ያ የሰማርያ ጥጃ፣ ተሰባብሮ ይደቅቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የተሠራው ነገር ከእስራኤል ዘንድ ነው፤ እርሱም በሞያተኛ የተሠራ ነው፤ እርሱም አምላክ አይደለም፤ የሰማርያም እምቦሳ ይሰባበራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይህ በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖት በአናጢ እጅ የተሠራ ስለ ሆነ አምላክ ሊሆን አይችልም፤ ስለዚህ በጥጃ ምስል የተሠራው የሰማርያ ጣዖት ተሰባብሮ ይወድቃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ይህ ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ነው፤ ሠራ​ተኛ ሠራው፤ እር​ሱም አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ርያ ሆይ! እን​ቦ​ሳሽ ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።

参见章节 复制




ሆሴዕ 8:6
22 交叉引用  

ደግሞም በቤቴል የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህን መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።


በሰማርያም ከተሞች የነበሩትን፥ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ የእስራኤል ነገሥታት የሠሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ኢዮስያስ አስወገዳቸው፤ በቤቴልም እንዳደረገው ነገር ሁሉ እንዲሁ አደረገባቸው።


አሁንም በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ ታስባላችሁ። እናንተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፤ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እምቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸው።


ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉን ፈጽመው እስካጠፉአቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፤ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።


ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ ሰንፎአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፥ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።


የእስራኤልም ቤት ይታመንባት ከነበረው ከቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ ከካሞሽ ያፍራል።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፥ አውሩ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፥ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ።


ልባቸው ተከፈለ፥ አሁንም በደላቸውን ይሸከማሉ፥ እርሱ መሠዊያቸውን ያፈርሳል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።


አሁንም ኃጢአትን ይሠሩ ዘንድ ጨመሩ፥ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፥ ሁሉም የሠራተኛ ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም፦ የሚሠው ሰዎች እምቦሳውን ይሳሙ ይላሉ።


አሦር አያድነንም፥ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፥ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም በሉት።


የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።


የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?


እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።


ይህም ጳውሎስ፦ በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል ሰምታችሁማል።


跟着我们:

广告


广告