Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንዳሰብሁ በልባቸው አያስቡም፥ አሁንም ሥራቸው ከብባቸዋለች፥ በፊቴም አለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣ እነርሱ አይገነዘቡም፤ ኀጢአታቸው ከብቧቸዋል፤ ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አላደረጉም፤ አሁንም ሥራዎቻቸው ከብበዋቸዋል፥ እነርሱም በፊቴ አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወን​ጀ​ላ​ቸ​ውን አንድ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው እንደ አሰቡ ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ዐሰ​ብሁ፤ አሁ​ንም ክፋ​ታ​ቸው ከብ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ በደ​ላ​ቸ​ውም በፊቴ አለች።

参见章节 复制




ሆሴዕ 7:2
33 交叉引用  

ዓይኖቹ በሰው መንገድ ላይ ናቸው፥ እርምጃውንም ሁሉ ያያል።


በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፥ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም።


አቤቱ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።


በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፥ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።


መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።


እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ መቅበዝበዝን ወድደዋል እግራቸውንም አልከለከሉም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፥ በደላቸውንም አሁን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።


ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፥ ከፊቴም አልተሰወሩም፥ ኃጢአታቸውም ከዓይኔ አልተሸሸገም።


የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብርዕና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፥ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾአል።


ክፋትሽ ይገሥጽሻል ክዳትሽም ይዘልፍሻል፥ አምላክሽንም እግዚአብሔርን የተውሽ እኔንም መፍራት የሌለብሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፥ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዓይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።


መንገድሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል፥ ይህ ክፋትሽ መራር ነው፥ ወደ ልብሽም ደርሶአል።


እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን?


ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።


እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፥ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ ሥራቸውንም እመልስባቸዋለሁ።


ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፥ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን።


መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፥ እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም፥ በደላቸውንም ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል፥ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፥ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፥ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፥ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።


በጊብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፥ እርሱም በደላቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይበቀላል።


እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ ሥራቸውን ሁሉ ለዘላለም ምንም አልረሳም።


እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ።


ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም።


ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


አእምሮ ቢኖራቸው፥ 2 ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ 2 ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር።


እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።


跟着我们:

广告


广告