Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በገላጣም ስፍራ ወንበዴ ቀምቶአልና፤ እስራኤልን በፈወስሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ሕዝቤን እስራኤልን ለመፈወስና እንደገናም እንዲበለጽጉ ለማድረግ በፈለግሁ ጊዜ የሕዝቡ በደልና የሰማርያ ክፋት ጐልቶ ይታያል፤ እርስ በርሳቸው ሐሰት ይናገራሉ፤ ቤት እየሰበሩ ይሰርቃሉ፤ በቡድን በቡድን ሆነው በየመንገዱ ይዘርፋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሐ​ሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ሌባም ገብ​ቶ​አ​ልና፥ በው​ጭም ወን​በ​ዴ​ዎች ቀም​ተ​ዋ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ውስ ዘንድ በወ​ደ​ድሁ ጊዜ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ትና የሰ​ማ​ርያ ክፋት ተገ​ለጠ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 7:1
30 交叉引用  

ለኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮ!


ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተንግረናል፥ አምላካችንንም ከመከተል ተመልሰናል፥ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፥ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።


ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፥ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።


ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሺቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።


ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ ሰማርያ ናት፥ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።


በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ አነጻሁሽ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።


የሰማርያ ሰዎች ስለ ቤትአዌን እምቦሳ ይፈራሉ፥ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም በኀዘን ይንተባተባሉ።


ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዩ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።


ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፥ ይሁዳም ከታመነው ቅዱሱ ከእግዚአብሔር ጋር አይጸናም።


ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።


ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፥ ተወው።


እርግማንና ሐሰት ግዳይና ስርቆት ምንዝርናም ወጥተዋል፥ ደምም ወደ ደም ደርሶአል።


ካህናት ሆይ፥ ይህን ስሙ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ አድምጡ፥ የንጉሥ ቤት ሆይ፥ ልብ አድርጉ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።


ምሕረታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ፥ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ፥ ምን ላድርግልህ?


ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐምፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ ልታደጋቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ።


ሰማርያ ሆይ፥ እምቦሳህን፥ ጥሎአል፥ ቍጣዬ በላያቸው ነድዶአል፥ እስከ መቼ ድረስ ንጹሕ ሊሆኑ አይችሉም?


ለብቻውም እንደሚቀመጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥተዋል፥ ኤፍሬምም ወዳጆቹን በእጅ መንሻ ገዛ።


ግፍንና ቅሚያን በአዳራሾቻቸው የሚያከማቹት ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አያውቁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


በአዛጦን አዳራሾችና በግብጽ ምድር አዳራሾች አውሩና፦ በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ውካታ፥ በመካከልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ በሉ።


በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉና፦ ዳን ሆይ፥ ሕያው አምላክህን! ደግሞ፦ ሕያው የቤርሳቤህን መንገድ! ብለው የሚሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ደግሞም አይነሡም።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፥ እናንተም አልወደዳችሁም።


እንዲህ እያለ፦ ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል።


跟着我们:

广告


广告