Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህ በነቢያት እጅ ቈረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው፥ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ በነቢያቴ ቈራረጥኋችሁ፤ በአፌም ቃል ገደልኋችሁ፣ ፍርዴም እንደ መብረቅ በላያችሁ አበራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ በነቢያት እጅ ቆረጥኋቸው፥ በአፌም ቃላት ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 6:5
35 交叉引用  

ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን?


እርስዋም በደጅ ስትገባ አኪያ የእግርዋን ኮቴ ሰማ፤ እንዲህም አለ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ! ግቢ፤ ስለ ምንስ ሌላ ሴት መሰልሽ? እኔም ብርቱ ወሬ ይዤ ተልኬልሻለሁ።


በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን “በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም፤” አለው።


አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ “እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?” አለው።


ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ፥ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።


ኤልያስም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም’” አለው።


ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣበት “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፤


ከጨለማ አይወጣም፥ ነበልባሉም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ አበባዎቹም ይረግፋሉ።


ስለዚህ እናንተ አእምሮ ያላችሁ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም ይሠራ ዘንድ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።


ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፥ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።


በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


እነሆ፥ ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ አድርጌሃለሁ አለኝ።


እነሆ፥ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።


በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸውማለች።


ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገርባቸው፥ ትንቢት ተናገር።


ከቡላድ ድንጋይ ይልቅ እንዳለ አልማዝ ግምባርህን አጠንክሬአለሁ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ቢሆኑ አትፍራቸው፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ብዛት ዋይ በል፥ እርስዋንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።


ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፥ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።


እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፥ ክፋትን አያደርግም፥ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፥ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።


ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል፦ ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ’ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።


የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤


በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።


እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።


የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።


ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።


ሳሙኤልም ሳኦልን፦ አላበጀህም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፥ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጽንቶልህ ነበር።


ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።


ሳሙኤልም፦ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፦ በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን? አለ።


ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።


跟着我们:

广告


广告