Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፥ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፥ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰባብሮናል፤ እርሱም ይጠግነናል፤ እርሱ አቍስሎናል፤ እርሱም ይፈውሰናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ይላሉ፦ “ኑ፥ ወደ ጌታ እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ኑ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! እርሱ እንደ ሰበረን ይፈውሰናል፤ እርሱ እንዳቈሰለን ቊስላችንን ይጠግናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 6:1
36 交叉引用  

እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።


በቍጣው ቀደደኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥ ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥


ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ብትዋረድም፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ ብታርቅ፥


በሕዝብ ወይም በሰው ዘንድ ቢሆን፥ እርሱ ቢያሳርፍ የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


እርሱ ይሰብራል፥ ይጠግንማል፥ ያቈስላል፥ እጆቹም ይፈውሳሉ።


ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፥ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥


በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፥ ዓይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።


ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ ወደ ጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።


በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፥ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ ወግዱ ትላቸውማለህ።


እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።


ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፥ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።


ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ፥ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስብራትህ የማይፈወስ ቍስልህም ክፉ ነው።


እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።


ከለዳውያን ለመዋጋት መጥተዋል፥ ነገር ግን በቍጣዬና በመዓቴ በገደልኋቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሉአቸው ነው፥ ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ሰውሬአለሁና።


እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፥ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ።


በዚያም ወራት በዚያም ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው ይመጣሉ፥ እያለቀሱም መንገዳቸውን ይሄዳሉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ።


ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ተጠጉ ብለው ስለ ጽዮን መንገድ ይጠይቃሉ።


መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ።


እግዚአብሔርን ይከተላሉ፥ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፥ ባገሣም ጊዜ ልጆች እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።


እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፥ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።


እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።


ቍጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፥ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።


ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።


እናንተ እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፥ ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ትኵሳት ሳይመጣባችሁ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፥ ተከማቹም።


አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ 2 ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ 2 እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ 2 እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ 2 ከእጄም የሚያድን የለም።


እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፥ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።


ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፦ በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው።


跟着我们:

广告


广告