Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በጊብዓ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉና፦ ብንያም ሆይ፥ ከአንተ በኋላ እያላችሁ በቤትአዌን ላይ እሪ በሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “በጊብዓ መለከትን፣ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤ ‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለጦርነት እንዲወጡ በገባዖን የመለከት፥ በራማም የጥሩንባ ድምፅ አሰሙ! በቤትአዌን “የብንያም ነገድ ሆይ! ከአንተ ጋር ነን” እያላችሁ ጩኹ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በኮ​ረ​ብታ ላይ መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ጩኹ፤ ብን​ያም በተ​ዋ​ረ​ደ​በት በቤ​ት​አ​ዌን ዐዋጅ ንገሩ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 5:8
20 交叉引用  

ካሰበው ሰው ልጆች ሰባት ሰዎች አሳልፈህ ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ ለእግዚአብሔር እንሰቅላቸዋለን አሉት። ንጉሡም፦ እሰጣችኋለሁ አለ።


አንዱን በቤቴል፥ ሁለተኛውንም በዳን አኖረ።


በመተላለፊያ አልፎአል፥ በጌባ ማደሪያው ነው፥ ራማ ደንግጣለች፥ የሳኦል ግብዓ ኰብልላለች።


በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፥ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።


እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።


የሰማርያ ሰዎች ስለ ቤትአዌን እምቦሳ ይፈራሉ፥ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም በኀዘን ይንተባተባሉ።


እስራኤል ሆይ፥ አንተ ብታመነዝር ይሁዳ አይበድል፥ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብላችሁ አትማሉ።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፥ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ንስር ይመጣል።


በጊብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፥ እርሱም በደላቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይበቀላል።


የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፥ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥


በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው፥ ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።


በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፥ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።


ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ፥


ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፥ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ ሳሙኤል ወደ አርማቴም መጡና፦


跟着我们:

广告


广告