Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፥ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቍስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቍስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እስራኤል መታመሙን፥ ይሁዳም መቊሰሉን ባየ ጊዜ፥ እስራኤል ወደ አሦር ፊቱን መለሰ፤ ርዳታም ለማግኘት ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ ነገር ግን እርሱ ሊያድናቸው ወይም ቊስላቸውን ሊፈውስ አልቻለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።

参见章节 复制




ሆሴዕ 5:13
16 交叉引用  

በዘመኑም የአሦር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም መንግሥቱን በእጁ ያጸናለት ዘንድ የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።


በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምን አገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሦርም አፈለሳቸው።


አካዝም “እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብን ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ፤” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ላከ።


በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፦ እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ባለ መድኃኒት አልሆንም፥ በሕዝቡም ላይ አለቃ አታደርጉኝም ይላል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስብራትህ የማይፈወስ ቍስልህም ክፉ ነው።


ኦሖላም ገለሞተችብኝ፥ ውሽሞችዋም ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው።


ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ወደ አሦር ይማረካል፥ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።


ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፥ ይሁዳም ከታመነው ቅዱሱ ከእግዚአብሔር ጋር አይጸናም።


አሦር አያድነንም፥ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፥ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም በሉት።


እናታቸው አመንዝራለች፥ የፀነሰቻቸውም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ ብላ አስነወረቻቸው።


ኤፍሬምም አእምሮ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፥ ግብጽን ጠሩ፥ ወደ አሦርም ሄዱ።


ለብቻውም እንደሚቀመጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥተዋል፥ ኤፍሬምም ወዳጆቹን በእጅ መንሻ ገዛ።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


跟着我们:

广告


广告