Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፥ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ ሥራቸውንም እመልስባቸዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፤ ስለ መንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ እንደ ሥራቸውም ብድራትን እከፍላቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ ካህናት እንደ ሕዝቡ ሆናችኋል፤ ስለዚህ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው ቅጣት በእናንተም በካህናት ላይ ይደርሳል፤ የክፉ ሥራችሁንም ብድራት ትከፍላላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እንደ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ካህኑ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 4:9
23 交叉引用  

እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፥ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፥ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፥ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፥ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፥ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።


የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁን፦ መልካም ይሆንልሃል በሉት።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፥ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።


በጣዖቶቻቸውም ፊት አገልግለዋቸው ነበሩና፥ ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋልና ስለዚህ እጄን በላያቸው አንሥቻለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይሸከማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እግዚአብሔርም፦ ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፥


በፈቀድሁም ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ፥ ስለ ሁለቱም ኃጢአታቸው በታሰሩ ጊዜ አሕዛብ ይሰበሰቡባቸዋል።


ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።


እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ክርክር አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፥ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።


እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንዳሰብሁ በልባቸው አያስቡም፥ አሁንም ሥራቸው ከብባቸዋለች፥ በፊቴም አለች።


መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፥ እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም፥ በደላቸውንም ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል፥ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፥ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፥ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፥ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።


በጊብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፥ እርሱም በደላቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይበቀላል።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።


跟着我们:

广告


广告