Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፥ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው፤ የመታሰቢያው ስም ጌታ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ እናንተ ወደ አምላካችሁ ተመለሱ፤ ፍቅርንና ትክክለኛ ፍትሕን አጥብቃችሁ ያዙ፤ አምላካችሁ እስኪረዳችሁ በትዕግሥት ጠብቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ሰ​ቢ​ያው ነው።

参见章节 复制




ሆሴዕ 12:6
39 交叉引用  

እግዚእብሔር ሆይ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ።


እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።


ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፥ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፥


እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፥ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።


እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።


እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለንም? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?


ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የመለሰውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፥ እተማመንበታለሁ።


በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።


እግዚአብሔር መጥቶ ጽድቅን እስኪያዘንብላችሁ ድረስ እርሱን የምትሹበት ዘመን ነውና ለእናንተ በጽድቅ ዝሩ፥ እንደ ምሕረቱም መጠን እጨዱ፥ ጥጋታችሁንም እረሱ።


እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።


ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።


እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም አሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።


ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።


ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?


እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አምላኬም ይሰማኛል።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፥ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፥ እርሱ አይዘገይም።


መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፥ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፥ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥


የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፥ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፥ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፥


ጴጥሮስም፦ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።


ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


跟着我们:

广告


广告