Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ወደ አሦር ይማረካል፥ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ ወደ አሦር ይወሰዳል፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም ደግሞ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ እንዲሆን ወደ አሦር ተማርኮ ይወሰዳል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጣዖቱ ወደ አሦር በመወሰድ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ሆኖ ይቀርባል፤ እስራኤል ከተከተለው ክፉ ምክር የተነሣ ኀፍረትና ውርደት ይደርስበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 10:6
22 交叉引用  

የአሦርም ንጉሥ ስልምናሶር በእርሱ ላይ ወጣ፤ ሆሴዕም ተገዛለት፤ ግብርም አመጣለት።


የኃይሉም እርምጃ ትጠብባለች፥ ምክሩም ትጥለዋለች።


በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁም፥ ስለ መረጣችኋትም አትክልት እፍረት ይይዛችኋልና፥


ስለዚህ የፈርዖን ኃይል እፍረት በግብጽም ጥላ መታመን ስድብ ይሆንባችኋል።


ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።


የእስራኤልም ቤት ይታመንባት ከነበረው ከቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ ከካሞሽ ያፍራል።


ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።


አልጠገብሽምና ከአሦራውያን ጋር ደግሞ ገለሞትሽ ከዚህም ጋር ገና አልጠገብሽም።


ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


አማልክቶቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎቻቸውን ከብርና ከወርቅም የተሠሩትን የከበሩትን ዕቃዎች ወደ ግብጽ ይማርካል፥ እስከ ጥቂትም ዓመት ድረስ ከሰሜን ንጉሥ ጋር ሳይዋጋ ይቀመጣል።


ነፋስ በክንፍዋ አስሮአታል፥ ከመሥዋዕታቸውም የተነሣ ያፍራሉ።


እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፥ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፥ እርሱ ግን ይፈውሳችሁ ዘንድ፥ ከቍስላችሁም ያድናችሁ ዘንድ አልቻለም።


ይህ ደግሞ ከእስራኤል ዘንድ ነው፥ ሠራተኛ ሠራው፥ እርሱም አምላክ አይደለም፥ የሰማርያም እምቦሳ ይቈራረጣል።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


跟着我们:

广告


广告