Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፥ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያውን አብዝቶአል፥ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ ብዙ ፍሬም አፈራ፤ ፍሬው በበዛ መጠን፣ ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ ምድሩ በበለጸገ መጠን፣ የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እስ​ራ​ኤል ፍሬው የበ​ዛ​ለት የለ​መ​ለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠ​ዊ​ያ​ዉን አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እንደ ምድ​ሩም ማማር መጠን ሐው​ል​ቶ​ችን ሠር​ተ​ዋል።

参见章节 复制




ሆሴዕ 10:1
24 交叉引用  

እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችንና ሐውልቶችን የማምለኪያ ዐፀዶችንም ለራሳቸው ሠሩ።


ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፥ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለነውረኛ ነገር መሠዊያ፥ እርሱም ለበኣል ታጥኑበት ዘንድ መሠዊያ፥ አድርጋችኋል።


ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።


ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


ለነቢያትም ተናግሬአለሁ፥ ራእይንም አብዝቻለሁ፥ በነቢያትም እጅ ምሳሌዎችን አውጥቻለሁ።


ከከነዓን ወገን ነው፥ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆን የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይመጣል፥ ምንጩንም ያደርቃል፥ ፈሳሹንም ያጠፋል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


አሁንም ኃጢአትን ይሠሩ ዘንድ ጨመሩ፥ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፥ ሁሉም የሠራተኛ ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም፦ የሚሠው ሰዎች እምቦሳውን ይሳሙ ይላሉ።


ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፥ ስለዚህ ረሱኝ።


እርስዋም እህልንና ወይንን ጠጅ ዘይትንም የሰጠኋት፥ ለበኣልም የተሠራውን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፥


እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፥ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።


ኤፍሬም ኃጢአትን ለመሥራት መሠዊያ አብዝቶአልና መሠዊያ ለኃጢአት ይሆንለታል።


ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፥ አለቆችንም አደረጉ፥ እኔም አላወቅሁም፥ ለጥፋታቸውም ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው አደረጉ።


እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።


ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።


ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።


跟着我们:

广告


广告