Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም፦ ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “በኢይዝራኤል ስለ ተፈጸመው ግድያ የኢዩን ቤት በቅርቡ ስለምቀጣና የእስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም ስለማደርግ፣ ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታም እንዲህ አለው፦ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ኢዩና ዘሮቹ በኢይዝራኤል በገደሉአቸው ሰዎች ምክንያት የኢዩን ቤተሰብ የምቀጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ የእስራኤልም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከጥ​ቂት ዘመን በኋላ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልን ደም በይ​ሁዳ ቤት ላይ እበ​ቀ​ላ​ለ​ሁና፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መን​ግ​ሥ​ትን እሽ​ራ​ለ​ሁና ስሙን ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ብለህ ጥራው፤

参见章节 复制




ሆሴዕ 1:4
32 交叉引用  

ለአክዓብም በሰማርያ ሰባ ልጆች ነበሩት፤ ኢዩም ደብዳቤ ጻፈ፤ የአክዓብን ልጆች ለሚያሳድጉ ለሰማርያ ታላላቆችና ሽማግሌዎች


ወደ ሰማርያም በመጣ ጊዜ ለኤልያስ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል እስኪያጠፋው ድረስ ከአክዓብ በሰማርያ የቀረውን ሁሉ ገደለ።


በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምን አገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሦርም አፈለሳቸው።


በይሁዳ ንጉሥ በዓዛርያስ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ስድስት ወር ነገሠ።


ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፥ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።


ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፥ እርስዋም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች።


ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፥ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።


በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፥ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ከዳተኛይቱም እስራኤል ስላመነዘረች ስለዚህ ፈትቻታለሁ የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ፥ አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን እንዳልፈራች እርስዋም ደግሞ ሄዳ እንደ ጋለሞተች አየሁ።


እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፥ ፍርድንም ስላደረጉባት በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች።


በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፥ ስለዚህ ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ።


ደግሞ ፀነሰች ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፦ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምርምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፥


እግዚአብሔርም፦ ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላክ አልሆናችሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው አለው።


ደስታዋንም ሁሉ፥ በዓላቶችዋንም፥ መባቻዎችዋንም፥ ሰንበቶችዋንም፥ የተቀደሱትንም ጉባኤዎችን ሁሉ አስቀራለሁ።


ለእኔም እንድትሆኚ በመታመን አጭሻለሁ፥ አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂአለሽ።


አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፥ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ።


እነሆ፥ የጌታ የእግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፥ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፥ ይላል እግዚአብሔር።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።


መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።


እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።


ብራናም ለምኖ፦ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።


እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።


ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥


跟着我们:

广告


广告