ዘፍጥረት 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ክዳን አነሣ፥ እነሆም ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ አንድ በሆነ ጊዜ፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፤ ምድሪቱ እንደ ደረቀች አየ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የኖኅ ዕድሜ 601 ዓመት በሆነ ጊዜ በመጀመሪያው ወር፥ በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፤ ምድሪቱ እንደ ደረቀች አየ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠራትን የመርከቢቱን ክዳን አነሣ፤ እነሆም፥ ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። 参见章节 |