Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኖኅ 600 ዓመት በሆነው ጊዜ፥ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ውሃ ምንጮች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፤ በሰማይ ያሉት የውሃ መስኮቶች ሁሉ ተከፈቱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥ በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 7:11
27 交叉引用  

እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ።


እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኂን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።


ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።


በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛውም ወር ቀን ምድር ደረቀች።


እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፉስን አሳለፈ፤ ውኂውም ጎደለ የቀላዪም ምንጮች የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፤


ያም አለቃ ለእግዚአብሔር ሰው መልሶ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ መስኮቶች ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” ብሎ ነበር፤ እርሱም “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያም አትቀምስም፤” ብሎት ነበር።


ንጉሡም በእጁ ተደግፎ የነበረ አለቃ ለእግዚአብሔር ሰው መልሶ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ መስኮቶች ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” አለው። እርሱም “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያም አትቀምስም፤” አለ።


እነሆ፥ ውኆቹን ይከለክላል፥ እነርሱም ይደርቃሉ። እንደ ገና ይሰዳቸዋል፥ ምድሪቱንም ይገለብጣሉ።


ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ ከሰውም እግር ተረሱ፥ ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ።


ወደ ባሕር ምንጭስ ውስጥ ገብተሃልን? በቀላዩስ መሠረት ውስጥ ተመላልሰሃልን?


የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው? ትቢያ በተበጠበጠ ጊዜ፥ ጓሎቹም በተጣበቁ ጊዜ፥ የሰማይን ረዋት ሊያዘነብል የሚችል ማን ነው?


የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፥ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሃት ድምጽ የሸሸ በገደል ይወድቃል፥ ከገ ደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።


ምድር ተሰባበረች፥ ምድር ፈጽማ ደቀቀች፥ ምድር ተነዋወጠች።


በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፥ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፥ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።


ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፥ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላዩንም ባወጣሁብሽ ጊዜ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፥ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።


በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤


跟着我们:

广告


广告