Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፦ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚን አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ አማላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፣ “እግዚአብሔር በረድኤቱ ያስባችኋል፤ በዚያ ጊዜ ዐፅሜን ከዚህ አገር ይዛችሁ እንድትወጡ” ሲል አስማላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፦ “እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ ብሎ” አስማላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር በሚጐበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐፅሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ዮሴ​ፍም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ አጥ​ን​ቴን ከዚህ አን​ሥ​ታ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማ​ላ​ቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:25
10 交叉引用  

አባቴ አምሎኛልን እንዲ ሲል፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ በቋፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።


ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ።


ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር ሳይጎበኛችሁ አይቀርም፤ አፅሜን ከዚህ ከእናንተ ጋር ታወጣላችሁ” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና ሙሴ የእርሱን አፅም ከእርሱ ጋር ወሰደ።


ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ፤ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ፤’ በላቸው።


ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው።


ዮሴፍ ወደ ሞት ቀርቦ ሳለ በእምነት ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት አስታወሰ፥ ስለ አጥንቱም አዘዛቸው።


የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በግ በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት፥ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።


እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።


跟着我们:

广告


广告