Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ እባክህ የውንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና አሁን እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉን ይቅር በል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ‘ለዮሴፍ፣ “ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኀጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው” ብላችሁ ንገሩት።’ አሁንም የእኛን የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኀጢአት ይቅር በለን።” መልእክታቸው ሲደርሰው ዮሴፍ አለቀሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ ‘እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፥ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፥ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባርያዎች የበደሉህን ይቅር በል።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ‘ወንድሞችህ በበደሉህ ጊዜ ያደረሱብህን ጒዳት ሁሉ አትቊጠርባቸው ብሎሃል’ ብለን እንድንነግርህ አዞናል፤ ስለዚህ እኛ የአባትህ አምላክ አገልጋዮች ያደረስንብህን በደል ሁሉ ይቅር እንድትለን እንለምንሃለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:17
24 交叉引用  

የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ድካም አየ፥ ትናንትም ገሠጸህ።


አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።


በአባትህ በአምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅ በረከት ከታች በሚሠራጭ በጡትና በማኅፀን በረከት።


ወደ ዮሴፍም መልእክት ላኩ እንዲህም አሉት፦ አባትህ ገና ሳይሞት እንዲህ ብሎ አዝዞአል፦


ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት።


እናንተ ክፋ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።


ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።


ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር።


እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።


በዚህም ሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን።


እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።


እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።


跟着我们:

广告


广告