Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፥ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:10
16 交叉引用  

ዔሳው፥ አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት ዔሳውም በልቡ አለ፦ ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል ከዚያም በኍላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።


በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ስዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ ይህ ለግብፅ ሰዎች ታልቅ ልቅሶ ነው አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት እርሱም በዮርዳኖች ማዶ ነው።


አርባ ቀንም ፈጸሙለት የሽቱ መደረጊያው ወራት እንደዚሁ ይፈጸማልን የግብፅም ሰዎች ሰባ ቅን አለቀሱለት።


የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዓን ቤተ ሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦


ሰረጎሎችም ፈረሶኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ ሠራዎቱም እጅግ ብዙ ነበረ።


ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኅዘን ቅኔ ተቀኘ፥


የኦርዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደሞተ በሰማች ጊዜ ለባልዋ አለቀሰች።


ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፤ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።


ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥


የሞተውን ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤


ማኅበሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእስራኤል ቤት ሁሉ ለአሮን ሠላሳ ቀን አለቀሱ።


በጸሎትም የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት።


በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በዓረባ ውስጥ በኤርትራ ባሕር ፊት ለፊት፥ በፋራን በጦፌልም በላባንም በሐጼሮትም በዲዛሃብም መካከል ሳሉ፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የነገራቸው ቃል ይህ ነው።


የእስራኤልም ልጆች በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።


አጥንታቸውንም ወሰዱ በኢያቢስም ባለው በአጣጡ ዛፍ በታች ቀበሩት፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።


跟着我们:

广告


广告