Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይሁዳ ወንድሞችህ አንተን ያመስግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንድስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤ እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፥ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፥ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ይሁዳ፥ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ አንገት ላይ ይበረታል፤ ወንድሞችህ በፊትህ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እጅ ይነሡሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “ይሁዳ፥ ወን​ድ​ሞ​ችህ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ እጅህ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ደን​ደስ ላይ ነው፤ የአ​ባ​ትህ ልጆች በፊ​ትህ ይሰ​ግ​ዳሉ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:8
38 交叉引用  

ለወንድሞችህ ጌት ሁን የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩም ይሁን።


ደግሞም ፀነስች ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።


ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት።


የይሁዳም ልጆች ዔር አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮችም ሐሙል።


የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።


ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፥ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፥ የይሁዳም ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።


የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፥ ንጉሡ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አደረገ፥ በእስራኤልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን ቀቡት።


ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ የዘላለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ ይሆን ዘንድ መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሠኝ ዘንድ ሊመርጠኝ ወደደ።


ይሁዳም በወንድሞቹ መካከል በረታ፤ አለቃም ከእርሱ ሆነ፤ ብኵርናው ግን ለዮሴፍ ነበረ።


ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት እና ጋሻ የሚሸከሙ፥ ቀስት የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።


አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴ፥ ከስምዖንም መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።


በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፤ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ።


ነገር ግን ከአሴርና ከምናሴ ከዛብሎንም አያሌ ሰዎች ሰውነታቸውን አዋረዱ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


ከይሁዳ ነገድ የተቈጠሩት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።


በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።


የይሁዳም ልጆች በየወገናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን።


እነዚህ የይሁዳ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።


የይሁዳ በረከት ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ 2 አቤቱ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ 2 ወደ ወገኖቹም አግባው፤ 2 እጆቹ ይጠንክሩለት፤ 2 በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ።


ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።


ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነውና፥ ስለዚህም ነገድ ሙሴ ምንም እንኳ ስለ ክህነት አልተናገረም።


እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የሰልፈኞች አለቆች፦ ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።


በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።


ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል


ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።


የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።


跟着我们:

广告


广告