Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በምክራቸው ነፍሴ፥ አትግባ ከጉባኤአቸውም ጋር ክብሬ አትተባበር በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክስዋልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወደ ሸንጓቸው አልግባ፤ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤ በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤ የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ፥ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር፥ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነርሱ በቊጣቸው ብዙ ወንዶችን ስለ ገደሉ፥ ከንቱ ምኞታቸውን ለማርካት ብዙ ኰርማዎችን ስለ ሰባበሩ፥ በእነርሱ ምክር አልገባም፤ የጉባኤውም ተካፋይ አልሆንም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በም​ክ​ራ​ቸው ሰው​ነቴ አት​ገ​ና​ኛ​ቸው፤ ዐሳ​ቤም በአ​መ​ፃ​ቸው አት​ተ​ባ​በ​ርም፤ በቍ​ጣ​ቸው ሰውን ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ በገዛ ፈቃ​ዳ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ርን ሥር ቈር​ጠ​ዋ​ልና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:6
29 交叉引用  

ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ እኔ በቁጥር ጥቂት ነኝ እነርሱ በእኔ ላይ ይስበሰቡና ይመቱኛል እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ


ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ያዘ፥ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፥ ለመቶ ሰረገላ ብቻ አስቀረ።


ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሃያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊትም ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሠረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቈረጠ።


በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፥ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።


አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፥ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።


ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።


ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?


ባልንጀራውን በስውር የሚመታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገባቸው፥ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።


ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ።


跟着我们:

广告


广告