Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሮቤል አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤ በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም ትበልጣለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥ የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል የምትበልጥ አንተ ነህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:3
17 交叉引用  

ልያም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።


እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ።


የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤


ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል።


ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው።


የእስራኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኵርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኵርና ጋር አልተቈጠረም።


የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ።


ከኤፍሬምም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሮቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።


የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥


የእስራኤል በኵር ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥


ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኩር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኩርነቱ የእርሱ ነው።


ይረግሙም ዘንድ እነዚህ፥ ሮቤልና ጋድ አሴርና ዛብሎን ዳንና ንፍታሌም፥ በጌባል ተራራ ላይ ይቁሙ።


ሮቤል በህይወት ይኑር፥ አይሙት፤ 2 ሰዎቹም በቁጥር ብዙ ይሁኑ፤


በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦


跟着我们:

广告


广告