Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:29 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሷል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ “እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ፥ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:29
16 交叉引用  

አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ።


አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።


በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና፤


እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።


በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን በሙሉ ዋጋ በመካከላችሁ ይስጠኝ፥ መቃብሩ የእኔ ርስት እንዲሆን።


ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ አብርሃምን ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት ወደ መምሬ ወደ ቂት ያትአርባቅ እርስዋም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።


ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠም፥ ሞተም ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።


ከአባቶቼም ጋር በተኛሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ በመቃብራቸውም ትቅብረኛለህ። እርሱም፦ እንደ ቃልህ አደርጋለሁ አለ።


እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።


ያዕቆብ ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹ በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።


ልጆቹም እንድዘዛቸው እንድዚያው አደረጉለት፤


ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጡያዊ ከኤፍሮን ከእርሽ ጋር የገዛት ዋሻ ናት


እኔ ባሪያህ ተመልሼ በከተማዬ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ፥ እባክህ፥ ልሙት። ነገር ግን ባሪያህን ከመዓምን እይ፥ እርሱ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም ለእርሱ አድርግ።


በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥


跟着我们:

广告


广告