Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 49:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በአባትህ በአምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅ በረከት ከታች በሚሠራጭ በጡትና በማኅፀን በረከት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥ ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤ ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የእኔ አም​ላክ ረዳህ፤ ከላይ በሰ​ማይ በረ​ከት፥ ሁሉ በሚ​ገ​ኝ​ባት፥ በም​ድር በረ​ከት፥ በጡ​ትና በማ​ኅ​ፀን በረ​ከት ባረ​ከህ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 49:25
22 交叉引用  

አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆን ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፥ እነሆ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጽምም ሁን፤


እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ


እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ፦ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤


የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤


ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥


ያዕቆብም አለ፦ የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፦ ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ


እግዚአብሔር አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።


ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ።


እርሱም አላቸው፦ ስላም ለእናንተ ይሁን አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል።


ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ ባረከኝም እንዲህም አለኝ፦


የሁለተኛውም ስም አልዓዛር ነበረ፦ የአባቴ አምላክ ረዳኝ፥ ከፈርዖንም ሰይፍ አዳነኝ ብሎአልና።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።


የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።


በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል።


አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


跟着我们:

广告


广告