Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 48:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እኔም ከመስዼጦምያ በመጣሁ ጊዜ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በመንገድ ሳለሁ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት ቀበርኍት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ መልስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፣ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ ዐዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እኔም ፓዳን በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት መንገድ ቀርቶኝ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፥ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ ቀበርኋት፥ እርሷም ቤተልሔም ናት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከመስጴጦምያ ስመለስ በከነዓን ምድር ገና ከኤፍራታ ሳልርቅ እናትህ ራሔል ሞተችብኝ፤ እርስዋን ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” (ይህችም ኤፍራታ ዛሬ ቤተልሔም ተብላ የምትጠራው ቦታ ነች።)

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እኔም ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍ​ራታ ለመ​ግ​ባት ጥቂት ቀር​ቶኝ በፈ​ረስ መጋ​ለ​ቢ​ያው መን​ገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከ​ነ​ዓን ምድር ሞተ​ች​ብኝ፤ በዚ​ያም በኤ​ፍ​ራታ ወደ ፈረስ መጋ​ለ​ቢያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ላይ ቀበ​ር​ኋት፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 48:7
13 交叉引用  

እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርይዊው የላባ እኅት ናት።


ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከንዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ።


ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው።


እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርይ ከተመለስ በኍላ እንደ ገና ተገለጠለት ባረከውም።


ከእነርሱም በኍላ የምትወልዳቸው ልጆች ለአንተ ይሁኑ በርስታቸው በወንድሞቻቸው ስም ይጠሩ።


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።


በተራራማው በኤፍሬም አገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ስሙ ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ነበረ፥ እርሱም የኢያሬምኤል ልጅ የኢሊዮ ልጅ የቶሑ ልጅ የናሲብ ልጅ ነበረ።


ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ዳርቻ በጼልጻህ አገር ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፥ እነርሱም፦ ልትሻቸው ሄደህ የነበርህላቸው አህዮች ተገኝተዋል፥ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ፥ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል።


ሳሙኤልም እግዚአብሔር የተናገረውን አደረገ፥ ወደ ቤተ ልሔምም መጣ። የአገሩም ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡና፦ የመጣኸው ለደኅንነት ነውን? አሉት።


ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፥ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፥ ስምንትም ልጆች ነበሩት፥ በሳኦልም ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።


跟着我们:

广告


广告