Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 48:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ ባረከኝም እንዲህም አለኝ፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን ቻይ አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ፥ ባረከኝም

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን አለው፥ “አም​ላኬ በከ​ነ​ዓን ምድር በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ ባረ​ከ​ኝም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 48:3
12 交叉引用  

አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆን ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፥ እነሆ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጽምም ሁን፤


እጅግም አበዛሃለሁ፥ ሕዝብም አደርግሃለሁም ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።


ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥


ለያዕቆብም፦ እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል ብለው ነገሩች እስራኤልም ተጠነካከረ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ።


በአባትህ በአምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅ በረከት ከታች በሚሠራጭ በጡትና በማኅፀን በረከት።


ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።


በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፥


የዮሴፍም ወገን ቤቴልን የሚሰልሉ ላኩ። አስቀድሞም የከተማይቱ ስም ሎዛ ይባል ነበር።


跟着我们:

广告


广告