Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 48:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው፥ የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ማድረጉን ባየ ጊዜ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 48:17
13 交叉引用  

የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደሆኑ ዔሳ ባየ ጊዜ፥


ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፋ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።


እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው እርሱም ታናሽ ነበረ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ ምናሴ በኵር ነበርና


ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው።


ዖምሪም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ከእርሱም አስቀድሞ ከነበሩት ይልቅ እጅግ ከፋ።


ከዚህም ነገር የተነሣ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ እስራኤልንም ቀሠፈ።


ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች።


በለዓምም የእግዚአብሔርን መልአክ፦ በድያለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ በፊቴ እንደቆምህብኝ አላወቅሁም፤ እንግዲህም አሁን አትወድድ እንደ ሆነ እመለሳለሁ አለው።


ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥


ለምናሴ ነገድ ዕጣ ይህ ነው፥ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ሰልፈኛ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።


እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፥ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፥ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።


跟着我们:

广告


广告