Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የግብፅ ምድር በፊትህ ናት በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር ይኑሩ ከእነርሱም ውስጥ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደ ሆነ በእንስሶቼ ላይ አለቆች አድርጋቸው

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የግብጽ ምድር እንደ ሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኀላፊዎች አድርጋቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የግብጽ ምድር በፊትህ ናት፥ በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፥ በጌሤም ምድር ይኑሩ፤ ከእነርሱ መካከል ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነሆ፥ መላው የግብጽ ምድር የአንተ ነው፤ ስለዚህ አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነችው በጌሴም ምድር እንዲኖሩ አድርግ። ከእነርሱ መካከል ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:6
24 交叉引用  

ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።


ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።


አቢሜሌክም፤ እነሆ ምድሬ በፊትህ ናት፤ በወደድኸው ተቀመጥ አለ።


ከእኝም ጋር ተቀመጡ ምድሪቱም በፊታችሁ ናት ኑሩባት ነግዱም ግዙአትም።


ወደ እኔ ና አትዘግይ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ ወደ እኔም ትቀርባለህ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፤


ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።


ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው።


ዮሴፍም፦ ከብቶቻችሁን አምጡልኝ ብር ካለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፋንታ እህል እሰጣችኍለሁ አለ።


ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።


ፈርዖንም ዮሴፍን ተናገረው እንዲህ ብሎ፦ አባትህና ወንድሞችን መጥተውልሃል


ኢዮርብዓምም ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ፤ ሰሎሞንም ጐልማሳው በሥራ የተመሰገነ መሆኑን ባየ ጊዜ በዮሴፍ ነገድ ሥራ ሁሉ ላይ ሾመው።


ብዙም እንስሶች ነበሩትና በምድረ በዳውና በቈላው በደጋውም ግንብ ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና አትክልተኞች ነበሩት።


አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።


ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ አዋቂዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶም አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የአሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።


ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቍስል ሆነ።


የእግዚአብሔርንም ቃል ያላሰበ ባሪያዎቹንና ከብቶቹን በሜዳ ተወ።


አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፥ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፥ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፥ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ።


በዚያም ቀን ከሳኦል ባሪያዎች አንድ ሰው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ተገኝቶ ነበር፥ ስሙም ኤዶማዊው ዶይቅ ነበረ፥ ለሳኦልም የእረኞቹ አለቃ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告