Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ምድሪቱን ዝሩ በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ሲሳይ ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከዐምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፤ ከዐምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፥ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ምግብ ይሁን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:24
14 交叉引用  

ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።


የሰዶም ንጉሥም አብራምን፤ ሰዎቹን ስጠኝ፥ ከብቱን ግን ለአንተ ውሰድ አለው።


ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።


ፈርዖን በምድር ላይ ሹማምትን ይሹም በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ፍሬ በግብፅ ምድር ሁሉ ከአምስት እጅ አንደኛውን ይውሰድ።


ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኍለሁ ዘር ውሰዱና


እርሱም፦ አንተ አዳንኸን በጌታችን ፊት ሞገስን አናግኝ ለፈርዖንም ባሪያዎች እንሆናለን አሉት።


የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።


ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ።


አሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው።


跟着我们:

广告


广告