Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የካህናትን ምድር ብቻ አልገዛም ካህናቱ ከፈርዖን የሰጣቸውን ድርጎ ይበሉ ነበር ስለዚህም ምድራቸውን አልሸጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሆኖም ዮሴፍ የካህናቱን መሬት አልገዛም፤ ምክንያቱም ካህናቱ ከፈርዖን ቋሚ ድርጎ ስለሚያገኙና ፈርዖን ከሚሰጣቸው ድርጎ በቂ ምግብ ስለ ነበራቸው ነው፤ ከዚህም የተነሣ መሬታቸውን አልሸጡም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የካህናትን ምድር ብቻ አልገዛም፥ ካህናቱ ከፈርዖን ዘንድ ድርጎ ያገኙ ነበርና፥ ፈርዖንም የሰጣቸውን ድርጎ ይበሉ ነበር፥ ስለዚህም ምድራቸውን አልሸጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዮሴፍ ያልገዛው የካህናቱን መሬት ብቻ ነው፤ ካህናት ከፈርዖን በየጊዜው ድርጎ ይቀበሉ ስለ ነበር መሬታቸውን ለመሸጥ አልተገደዱም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዮሴፍ የካ​ህ​ና​ትን ምድር ብቻ አል​ገ​ዛም፤ ፈር​ዖን ለካ​ህ​ናቱ ድርጎ ይሰ​ጣ​ቸው ነበ​ርና፥ ፈር​ዖ​ንም የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን አል​ሸ​ጡም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:22
16 交叉引用  

የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።


ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ።


ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት።


ሕዝቡንም ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ አንሥቶ እስከ ሌላው ዳርቻዋ ድረስ ባርያዎች አደረጋቸው።


ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኍለሁ ዘር ውሰዱና


ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዓን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሕግ አደረጋት።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ።


ደግሞም በካህናቱና በሌዋውያን፥ በመዘምራኑ፥ በበረኞቹና በናታኒም፥ በዚህም በእግዚአብሔር ቤት በሚሠሩ አገልጋዮች ላይ ግብርና ቀረጥ፥ መጥንም እንዳይጣል ብለን እናስታውቃችኋለን።’


ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ።


ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን?


ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።


በምድርህ ላይ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ።


ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን፦ ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና።


በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


跟着我们:

广告


广告