Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዮሴፍም ገባ ለፈርዖንም ነገረው እንዲህ ብሎ፦ አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውም ላሞቻቸውም ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር ወጡ እነርሱም እነሆ በጌሤም ምድር ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:1
8 交叉引用  

ወደ እኔ ና አትዘግይ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ ወደ እኔም ትቀርባለህ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፤


በፈርዖን ቤት፦ የዮሴፍ ወንድሞች መጡ ተብሎ ወሬ ተሰማ በዚያውም ፈርዖንና ሎላልቱ ደስ ተሰኙበት።


ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍም ላከ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ።


ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ስዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤


ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።


በዚያን ቀን በምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የዝንብ መንጋ እንዳይሆን ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጌሤምን ምድር እለያለሁ።


የእስራኤል ልጆች ተቀምጠው በነበሩባት በጌሤም አገር ብቻ በረዶ አልወረደም።


የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና፤


跟着我们:

广告


广告