Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 46:34 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እናንተ፣ ‘እኛ ባሮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከዚያም ግብጻውያን ከብት አርቢዎችን እንደ ጸያፍ ስለሚቈጥሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 46:34
17 交叉引用  

የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።


አብራምም ሎጥን አለው እኛ ወንድማምች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ።


የጌራራ አገር እረኞች ለይስሐቅ እረኞች ጋር፦ ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ፤ የዚይችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና።


በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ ከበጎቹም መካከል ጥኩሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።


ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።


ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ።


የያዕቆብም ትውልድ ይህ ነው። ዮሴፍ የአሥራ ሰባት ዓመት ልጅ በሆን ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር በጎችን ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክራታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው አመጣ።


ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።


ወደ እኔ ና አትዘግይ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ ወደ እኔም ትቀርባለህ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፤


ሂዱ አባታችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁም ወደ እኔ ኑ እኔም የግብፅን ምድር በረከት ሁሉ እሰጣችኍለሁ፥ የምድሪቱንም ስብ ትበላላችሁ።


እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው እነርስሳ ያረቡ ነበርና በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ።


ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው።


ፈርዖንም ወንድሞቹም፦ ሥራችሁ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ እኛ ባሪያዎችን እኝም አባቶቻችንም በግ አርቢዎች ነን አሉት።


ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።


የግብፅ ምድር በፊትህ ናት በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር ይኑሩ ከእነርሱም ውስጥ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደ ሆነ በእንስሶቼ ላይ አለቆች አድርጋቸው


በዚያን ቀን በምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የዝንብ መንጋ እንዳይሆን ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጌሤምን ምድር እለያለሁ።


ሙሴም፦ “ለእግዚአብሔር ለአምላካችን የግብፃውያንን ርኩሰት እንሰዋለንና እንዲህ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ እነሆ እኛ የግብፃውያንን ርኵሰት በፊታቸው ብንሠዋ አይወግሩንምን?


跟着我们:

广告


广告